| ← Nehemiah (7/13) → |
| 1. | እንዲህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ ሳንቃዎቹንም ካቆምሁ በኋላ፥ በረኞቹና መዘምራኑ ሌዋውያኑም ከተሾሙ በኋላ፥ |
| 2. | ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። |
| 3. | እኔም። ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፤ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፤ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው። |
| 4. | ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር። |
| 5. | አምላኬም ታላቆቹንና ሹማምቱን ሕዝቡንም ሰብስቤ እቈጥራቸው ዘንድ በልቤ አደረገ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ። |
| 6. | የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። |
| 7. | ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከአዛርያስ፥ ከረዓምያ፥ ከነሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከሚስጴሬት፥ ከበጉዋይ፥ ከነሑም፥ ከበዓና ጋር መጡ። |
| 8. | የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። |
| 9. | የሰፋጥያስ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። |
| 10. | የኤራ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት። |
| 11. | ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ስምንት። |
| 12. | የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። |
| 13. | የዛቱዕ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት። |
| 14. | የዘካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ። |
| 15. | የቢንዊ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት። |
| 16. | የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት። |
| 17. | የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት። |
| 18. | የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት። |
| 19. | የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። |
| 20. | የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት። |
| 21. | የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። |
| 22. | የሐሱም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት። |
| 23. | የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት። |
| 24. | የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት። |
| 25. | የገባዖን ልጆች፥ ዘጠና አምስት። |
| 26. | የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት። |
| 27. | የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። |
| 28. | የቤትዓዝሞት ሰዎች፥ አርባ ሁለት። |
| 29. | የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። |
| 30. | የራማና የጌባ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። |
| 31. | የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። |
| 32. | የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሦስት። |
| 33. | የሁለተኛው ናባው ሰዎች፥ አምሳ ሁለት። |
| 34. | የሁለተኛው ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። |
| 35. | የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። |
| 36. | የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት |
| 37. | የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ። |
| 38. | የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ። |
| 39. | ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። |
| 40. | የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት። |
| 41. | የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። |
| 42. | የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት። |
| 43. | ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። |
| 44. | መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ አርባ ስምንት። |
| 45. | በረኞቹ፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ መቶ ሠላሳ ስምንት። |
| 46. | ናታኒም፥ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ |
| 47. | የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ |
| 48. | የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ |
| 49. | የአጋባ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ |
| 50. | የራያ ልጆች፥ የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ |
| 51. | የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ |
| 52. | የቤሳይ ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ |
| 53. | የንፉሰሲም ልጆች፥ የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቀፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ |
| 54. | የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ |
| 55. | የበርቆስ ልጆች፥ የሲሣራ ልጆች፥ |
| 56. | የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። |
| 57. | የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ |
| 58. | የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ |
| 59. | የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈከራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች። |
| 60. | ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። |
| 61. | ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤ |
| 62. | የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። |
| 63. | ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። |
| 64. | እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። |
| 65. | ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር አትበሉም አላቸው። |
| 67. | ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ሁለቱ መቶም አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። |
| 68. | ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት፥ በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ |
| 69. | ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ። |
| 70. | ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ ሰዎች ስለ ሥራው ስጦታ ሰጡ። ሐቴርሰታም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳም ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳም የካህናት ልብስ በቤተ መዛግብት ውስጥ ሰጠ። |
| 71. | ከአባቶች ቤቶች አለቆችም አያሌዎቹ በሥራው ቤተ መዛግብት ውስጥ ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶም ምናን ብር ሰጡ። |
| 72. | የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ። |
| 73. | ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |
| ← Nehemiah (7/13) → |