| ← Nehemiah (12/13) → |
| 1. | ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር የወጡት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ |
| 2. | ሠራያ፥ ኤርምያስ፥ ዕዝራ፥ አማርያ፥ |
| 3. | መሉክ፥ ሐጡስ፥ ሴኬንያ፥ ሬሁም፥ ሜሪሞት፥ |
| 5. | አዶ፥ ጌንቶን፥ አብያ፥ ሚያሚን |
| 6. | መዓድያ፥ ቢልጋ፥ ሸማያ፥ ዮያሪብ፥ ዮዳኤ፥ |
| 7. | ሰሉ፥ ዓሞቅ፥ ኬልቅያስ፥ ዮዳኤ፤ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቻቸው አለቆች ነበሩ። |
| 8. | ሌዋውያኑም፤ ኢያሱ፥ ቢንዊ፥ ቀድምኤል፥ ሰራብያ፥ ይሁዳ፥ ከወንድሞቹም ጋር በመዘምራን ላይ የነበረ መታንያ። |
| 9. | ወንድሞቻቸውም በቅቡቅያና ዑኒ በየሰሞናቸው በአንጻራቸው ነበሩ። |
| 10. | ኢያሱም ዮአቂምን ወለደ፥ ዮአቂምም ኤልያሴብን ወለደ፥ ኤልያሴብም ዮአዳን ወለደ፥ |
| 11. | ዮአዳም ዮናታንን ወለደ፥ ዮናታንም ያዱአን ወለደ። |
| 12. | በዮአቂምም ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች እነዚህ ካህናቱ ነበሩ፤ ከሠራያ ምራያ፥ |
| 13. | ከኤርምያስ ሐናንያ፥ ከዕዝራ ሜሱላም፥ |
| 14. | ከአማርያ ይሆሐናን፥ ከመሉኪ ዮናታን፥ |
| 15. | ከሰበንያ ዮሴፍ፥ ከካሪም ዓድና፥ ከመራዮት ሔልቃይ፥ |
| 16. | ከአዶ ዘካርያስ፥ ከጌንቶን ሜሱላም፥ |
| 17. | ከአብያ ዚክሪ፥ ከሚያሚን ሞዓድያ፥ |
| 18. | ፈልጣይ፥ ከቢልጋ ሳሙስ፥ ከሸማያ ዮናታን፥ |
| 19. | ከዮያሪብ መትናይ፥ ከዮዳኤ ኦዚ፥ |
| 20. | ከሳላይ ቃላይ፥ ከዓሞቅ ዔቤር፥ |
| 21. | ከኬልቅያስ ሐሸብያ፥ ከዮዳኤ ናትናኤል። |
| 22. | ከሌዋውያኑም በኤልያሴብና በዮአዳ፥ በዮሐናንና በያዱአ ዘመን የአባቶች ቤቶች አለቆች ተጻፉ፤ ካህናቱም በፋርሳዊው በዳርዮስ መንግሥት ዘመን ተጻፉ። |
| 23. | የሌዊ ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች እስከ ኤልያሴብ ልጅ እስከ ዮሐናን ዘመን ድረስ በታሪክ መጽሐፍ ተጻፉ። |
| 24. | የሌዋውያኑም አለቆች፤ ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር። |
| 25. | መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዮ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ። |
| 26. | እነዚህ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮአቂም በአለቃውም በነህምያ በጸሐፊውም በካህኑ በዕዝራ ዘመን ነበሩ። |
| 27. | የኢየሩሳሌምንም ቅጥር በቀደሱ ጊዜ ቅዳሴውን በደስታና በምስጋና በመዝሙርም በጸናጽልም በበገናም በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ። |
| 29. | መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና የመዘምራኑ ልጆች ከኢየሩሳሌም ዙሪያና ከነጦፋውያን መንደሮች፥ ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ። |
| 30. | ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ። |
| 31. | የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፤ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፤ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄደ። |
| 32. | ከእነርሱም በኋላ ሆሻያ፥ የይሁዳም አለቆች እኵሌታ፥ |
| 33. | ዓዛርያስ፥ ዕዝራ፥ |
| 34. | ሜሱላም፥ ይሁዳ፥ ብንያም፥ ሸማያ፥ ኤርምያስ፥ |
| 35. | መለከትም ይዘው ከካህናቱ ልጆች አያሌዎች፥ የአሳፍም ልጅ የዘኩር ልጅ የሚካያ ልጅ የመታንያ ልጅ የሸማያ ልጅ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥ |
| 36. | ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ። |
| 37. | በምንጭም በር አቅንተው ሄዱ፤ በዳዊትም ከተማ ደረጃ፥ በቅጥሩም መውጫ፥ ከዳዊትም ቤት በላይ እስከ ውኃው በር ድረስ በምሥራቅ በኩል ሄዱ። |
| 38. | ሁለተኛውም የአመስጋኞቹ ተርታ ወደ ግራ ሄደ፤ እኔና የሕዝቡም እኵሌታ በስተኋላቸው ነበርን፤ በቅጥሩም ላይ፥ በእቶኑ ግንብ በላይ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ፥ ከኤፍሬምም በር በላይ፥ |
| 39. | በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። |
| 40. | እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኵሌታ፥ |
| 41. | ካህናቱም ኤልያቄም፥ መዕሤያ፥ ሚንያሚን፥ ሚካያ፥ ኤልዮዔናይ፥ |
| 42. | ዘካርያስ፥ ሐናንያ መለከት ይዘው፥ መዕሤያ፥ ሸማያ፥ አልዓዛር፥ ኦዚ፥ ይሆሐናን፥ መልክያ፥ ኤላም፥ ኤጽር ቆምን። መዘምራኑም በታላቅ ድምፅ ዘመሩ፥ አለቃቸውም ይዝረሕያ ነበረ። |
| 43. | እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ። |
| 44. | ይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቍርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ። |
| 45. | እነርሱም መዘምራኑና በረኞቹም የአምላካቸውን ሥርዓት የመንጻታቸውንም ሥርዓት እንደ ዳዊትና እንደ ልጁ እንደ ሰሎሞን ትእዛዝ ጠበቁ። |
| 46. | አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ። |
| 47. | እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ። |
| ← Nehemiah (12/13) → |