| ← Nehemiah (11/13) → |
| 1. | የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ። |
| 2. | ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ። |
| 3. | በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የአገሩ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም ሌዋውያኑም ናታኒምም የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ። |
| 4. | ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ አታያ፤ |
| 5. | የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ። |
| 6. | በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ። |
| 7. | የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ። |
| 8. | ከእርሱም በኋላ ጌቤና ሳላይ ዘጠኝ መቶም ሀያ ስምንት። |
| 9. | አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሐስኑአም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። |
| 10. | ከካህናቱ፤ የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፥ ያኪን፥ |
| 11. | የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፥ |
| 12. | የቤቱንም ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሀያ ሁለት፤ የመልክያ ልጅ የፋስኮር ልጅ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፥ |
| 13. | ወንድሞቹም የአባቶቹ ቤቶች አለቆች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ የአሕዛይ ልጅ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፥ |
| 14. | ወንድሞቻቸውም መቶ ሀያ ስምንት ጽኑዓን ኃያላን፤ አለቃቸውም የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበረ። |
| 15. | ከሌዋውያንም፤ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሻማያ፤ |
| 16. | ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሳባታይና ዮዛባት፤ |
| 17. | በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ። |
| 18. | በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ። |
| 19. | በሮቹንም የሚጠብቁ በረኞቹ፥ ዓቁብና ጤልሞን ወንድሞቻቸውም፥ መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ። |
| 20. | ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ። |
| 21. | ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር፤ ሲሐና ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ። |
| 22. | በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ። |
| 23. | ስለ እነርሱም የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፤ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ። |
| 24. | ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ። |
| 25. | ስለ መንደሮቹና ስለ እርሾቻቸው፤ ከይሁዳ ልጆች አያሌዎች በቂርያትአርባቅና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋም፥ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋም፥ |
| 27. | በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል፥ |
| 28. | በቤርሳቤህና በመንደሮችዋ፥ በጺቅላግ፥ |
| 29. | በምኮናና በመንደሮችዋ፥ በዓይንሪሞን፥ |
| 30. | በጾርዓ፥ በየርሙት፥ በዛኖዋ በዓዶላም በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። |
| 31. | የብንያምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማክማስ፥ በጋያ፥ |
| 32. | በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ በዓናቶት፥ በኖብ፥ |
| 34. | በሐናንያ፥ በሐጾር፥ በራማ፥ በጊቴም፥ በሐዲድ፥ |
| 35. | በስቦይም፥ በንበላት፥ በሎድ፥ በኦኖ፥ በጌሐራሺም ተቀመጡ። |
| 36. | በይሁዳም ከነበሩ ሌዋውያን አያሌ ክፍሎች ወደ ብንያም ሆኑ። |
| ← Nehemiah (11/13) → |