| ← Job (35/42) → |
| 1. | ኤሊሁም ደግሞ መለሰ እንዲህም አለ። |
| 2. | ይህ ጽድቅ እንደ ሆነ ታስባለህን? ወይስ። በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን? |
| 3. | አንተ። ምን ጥቅም አለህ? ኃጢአት ሠርቼ ከማገኘው ይልቅ ኃጢአት ባልሠራ ኖሮ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቀሃልና። |
| 4. | እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ እመልሳለሁ። |
| 5. | ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፤ ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት። |
| 6. | ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ? |
| 7. | ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል? |
| 8. | እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፤ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል። |
| 9. | ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፤ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጠራሉ። |
| 11. | ነገር ግን። በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፥ ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረን ከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን፤ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም። |
| 12. | በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። |
| 13. | በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፤ |
| 14. | ይልቁንም። አላየውም፤ ነገሩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ ስትል። |
| 15. | አሁን ግን በቍጣው አልጐበኘምና። በኃጢአት እጅግ አያስብም ትላለህ። |
| 16. | ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፥ ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል። |
| ← Job (35/42) → |