| ← Job (25/42) → |
| 1. | ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ። |
| 2. | ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው። |
| 3. | በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው? |
| 4. | ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል? |
| 5. | እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። |
| 6. | ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ! |
| ← Job (25/42) → |