← Ezra (2/10) → |
1. | የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። |
2. | ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዕላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከበላሳን፥ ከመሴፋር፥ ከበጉዋይ፥ ከሬሁም፥ ከበዓና ጋር መጡ። |
3. | የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው፤ የፋሮስ ልጆች፥ ሁለት ሺህ መቶ ሰባ ሁለት። |
4. | የሰፋጥያስ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። |
5. | የኤራ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሰባ አምስት። |
6. | ከኢያሱና ከኢዮአብ ልጆች የሆኑ የፈሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አሥራ ሁለት። |
7. | የኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። |
8. | የዛቱዕ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት። |
9. | የዘካይ ልጆች ሰባት መቶ ስድሳ። |
10. | የባኒ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። |
11. | የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ሦስት። |
12. | የዓዝጋድ ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ ሀያ ሁለት። |
13. | የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት። |
14. | የበጉዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አምሳ ስድስት። |
15. | የዓዲን ልጆች፥ አራት መቶ አምሳ አራት። |
16. | ከሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። |
17. | የቤሳይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ሦስት። |
18. | የዮራ ልጆች፥ መቶ አሥራ ሁለት። |
19. | የሐሱም ልጆች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። |
21. | የጋቤር ልጆች፥ ዘጠና አምስት። የቤተ ልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት። |
22. | የነጦፋ ሰዎች፥ አምሳ ስድስት። |
23. | የዓናቶት ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። |
24. | የዓዝሞት ልጆች፥ አርባ ሁለት። |
25. | የቂርያትይዓሪምና የከፊራ የብኤሮትም ልጆች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። |
26. | የራማና የጌባ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። |
27. | የማክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። |
28. | የቤቴልና የጋይ ሰዎች፥ ሁለት መቶ ሀያ ሦስት። |
29. | የናባው ልጆች፥ አምሳ ሁለት። |
30. | የመጌብስ ልጆች፥ መቶ አምሳ ስድስት። |
31. | የሁለተኛውም ኤላም ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። |
32. | የካሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። |
33. | የሎድና የሐዲድ የኦኖም ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አምስት። |
34. | የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት። |
35. | የሴናዓ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ። |
36. | ካህናቱ፤ ከኢያሱ ወገን የዮዳኤ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። |
37. | የኢሜር ልጆች፥ ሺህ አምሳ ሁለት። |
38. | የፋስኮር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። |
39. | የካሪም ልጆች፥ ሺህ አሥራ ሰባት። |
40. | ሌዋውያኑ፤ ከሆዳይዋ ወገን የኢያሱና የቀድምኤል ልጆች፥ ሰባ አራት። |
41. | መዘምራኑ፤ የአሳፍ ልጆች፥ መቶ ሀያ ስምንት። |
42. | የበረኞች ልጆች፤ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች፥ ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ። |
43. | ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ |
44. | የጠብዖት ልጆች፥ የኬራስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፤ |
45. | የፋዶን ልጆች፥ የልባና ልጆች፥ |
46. | የአጋባ ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የአጋብ ልጆች፥ የሰምላይ ልጆች፥ የሐናን ልጆች፥ |
47. | የጌዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ የራያ ልጆች፥ |
48. | የረአሶን ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ |
49. | የጋሴም ልጆች፥ የዖዛ ልጆች፥ የፋሴሐ ልጆች፥ |
50. | የቤሳይ ልጆች፥ የአስና ልጆች፥ የምዑናውያን ልጆች፥ የንፉሰሲም ልጆች፥ |
51. | የበቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ |
52. | የበስሎት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ |
53. | የሐርሳ ልጆች፥ የበርቆስ ልጆች፥ |
54. | የሲሣራ ልጆች፥ የቴማ ልጆች፥ የንስያ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች። |
55. | የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፍሩዳ ልጆች፥ |
56. | የየዕላ ልጆች፥ የደርቆን ልጆች፥ የጌዴል ልጆች፥ |
57. | የሰፋጥያስ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፈክራት ልጆች፥ የሐፂቦይም ልጆች፥ የአሚ ልጆች። |
58. | እነዚህ ናታኒም ሁሉና የሰሎሞን ባሪያዎች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ። |
59. | ከቴልሜላ፥ ከቴላሬሳ፥ ከክሩብ፥ ከአዳን፥ ከኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ያስታውቁ ዘንድ አልቻሉም፤ |
60. | የዳላያ ልጆች፥ የጦብያ ልጆች፥ የኔቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት ነበሩ። |
61. | ከካህናቱም ልጆች፤ የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች። |
62. | እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አልተገኘም፥ ከክህነትም ተከለከሉ። |
63. | ሐቴርሰታም። በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ድረስ ከቅዱሰ ቅዱሳን አትበሉም አላቸው። |
65. | ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ጉባኤው ሁሉ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበሩ። ሁለት መቶም ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። |
66. | ፈረሶቻቸውም ሰባት መቶ ሠላሳ ስድስት በቅሎቻቸውም ሁለት መቶ አርባ አምስት፥ |
67. | ግመሎቻቸውም አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸውም ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ። |
68. | በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠራ ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ። |
69. | ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። |
70. | ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹም፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |
← Ezra (2/10) → |