← Exodus (11/40) → |
1. | እግዚአብሔርም ሙሴን። በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሰፍት አመጣለሁ፥ ከዚያ ወዲያም ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም አባርሮ ይሰድዳችኋል። |
2. | ወንዱ ከወዳጁ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ ይሹ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ ተናገር አለው። |
3. | እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠው። ሙሴም በፈርዖን ባሪያዎችና በሕዝቡ ፊት በግብፅ አገር እጅግ የከበረ ሰው ነበረ። |
4. | ሙሴም አለ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በእኩል ሌሊት እኔ በግብፅ መካከል እወጣለሁ፤ |
5. | በግብፅም አገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል። |
6. | በግብፅም አገር ሁሉ አስቀድሞ እንደ እርሱ ያልሆነ ኋላም ደግሞ የማይሆን ታላቅ ጩኸት ይሆናል። |
7. | እግዚአብሔር ግን በግብፃውያንና በእስራኤል መካከል እንዲለይ እንድታውቁ በእስራኤል ልጆች መካከል ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ውሻ ምላሱን አያንቀሳቅስባቸውም። |
8. | እነዚህም ባሪያዎችህ ሁሉ። አንተ ውጣ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፥ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ። ሙሴም በጽኑ ቁጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ። |
9. | እግዚአብሔርም ሙሴን። ተአምራቴ በግብፅ አገር ብዙ እንዲሆን ፈርዖን አይሰማችሁም አለው። |
10. | ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፥ የእስራኤልንም ልጆች ከአገሩ አልለቀቀም። |
← Exodus (11/40) → |