| ← Esther (10/10) |
| 1. | ንጉሡም አርጤክስስ በምድርና በባሕር ደሴቶች ላይ ግብር ጣለ። |
| 2. | የኃይሉና የብርታቱም ሥራ ሁሉ ንጉሡም እስከ ምን ድረስ እንዳከበረው የመርዶክዮስ ክብር ታላቅነት፥ በሜዶንና በፋርስ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
| 3. | አይሁዳዊውም መርዶክዮስ ለንጉሡ ለአርጤክስስ በማዕርግ ሁለተኛ ነበረ፤ በአይሁድም ዘንድ የከበረ፥ በብዙ ወንድሞችም ዘንድ የተወደደ፥ ለሕዝቡም መልካምን የፈለገ፥ ለዘሩም ሁሉ በደኅና የተናገረ ነበረ። |
| ← Esther (10/10) |