| ← 1Chronicles (3/29) → |
| 1. | በኬብሮንም ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥ |
| 2. | ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥ |
| 3. | አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትረኃም ከሚስቱ ከዔግላ። |
| 4. | ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። |
| 5. | እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ |
| 6. | ሰሎሞን፥ አራት፤ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥ |
| 7. | ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ |
| 8. | ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት፥ ዘጠኝ። |
| 9. | እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች። |
| 10. | የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ |
| 11. | ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥ ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ |
| 12. | ልጁ አሜስያስ፥ ልጁ ዓዛርያስ፥ ልጁ ኢዮአታም፥ |
| 13. | ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥ |
| 14. | ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮስያስ። |
| 15. | የኢዮስያስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም። |
| 16. | የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያን፥ ልጁ ሴዴቅያስ። |
| 17. | የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ መልኪራም፥ |
| 18. | ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ። |
| 19. | የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት። |
| 20. | ሐሹባ፥ ኦሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ፥ ዮሻብሒሴድ አምስት ናቸው። |
| 21. | የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች። |
| 22. | የሴኬንያም ልጅ ሸማያ ነበረ። የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግኣል፥ ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ። |
| 23. | የነዓርያም ልጆች ኤልዮዔናይ፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዝሪቃም ሦስት ነበሩ። |
| 24. | የኤልዮዔናይም ልጆች ሆዳይዋ፥ ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ። |
| ← 1Chronicles (3/29) → |