1Chronicles (25/29)  

1. ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
2. ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ እጅ በታች ነበሩ።
3. ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም እጅ በታች ነበሩ።
4. ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት፤
5. እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን አሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።
6. እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ ከአባታቸው እጅ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።
7. የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
8. ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪውም እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።
9. የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም አሥራ ሁለት ነበሩ፤
10. ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
11. አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
12. አምስተኛው ለነታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
13. ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
14. ሰባተኛው ለይሽርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
15. ስምንተኛው ለየሻያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
16. ዘጠኝኛው ለመታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
17. አሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
18. አሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
19. አሥራ ሁለተኛው ለሐሸብያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
20. አሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
21. አሥራ አራተኛው ለመቲትያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
22. አሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
23. አሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
24. አሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25. አሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
26. አሥራ ዘጠኝኛው ለመሎቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
27. ሀያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
28. ሀያ አንደኛው ለሆቲር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
29. ሀያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
30. ሀያ ሦስተኛው ለመሐዚዮት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
31. ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ ወጣ።

  1Chronicles (25/29)